ዩኒቲ ዩንቨርሲቲ

ዩኒቲ ዩንቨርስቲ ለ 2013 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ፣ በአዳማ ና በደሴ ከሚገኙ ካምፓሶች 2,200 ተማሪዎችን ማስመረቁን ገልፀዋል።ዩኒቨርስቲው በአዲስ አበባ በአዳማ እና ደሴ ካምፓሶቹ በ መጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ መርሀግብሮች ያሰለጠናቸው ተማሪዎች ሲሆኑ ዛሬ የተመረቁት፤ 56 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ገልፀዋል ።በአዲስ አበባ አል-አሙዲ ካምፓስ በተከናወነው የምርቃት ስነስርዓት ከካምፓሱ ተማሪዎች በተጨማሪ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የምርቃት ስነስርዓታቸውን ማከናወን ያልቻሉ የዩኒቨርስቲው የደሴ ካምፓስ ተማሪዎች ተገኝተዋል።ዩኒቨርስቲው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በአጠቃላይ ከ60ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ ደረጃዎች አስመርቋል።ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram: https://t.me/ebstvworldwideFollow us on: https://linktr.ee/ebstelevision#ኢቢኤስ#EBS