EthiopiaLatestNews

14 የንግድ መገናኛ ብዙሀን ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውሉ ድጋፎችን አስረከቡ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ 14 የንግድ መገናኛ ብዙሀን በሰሜኑ የሀገራችን ጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውሉ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዛሬ አስረክበዋል።በኢትዮጵያ ብሮድካስት ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባል የሆኑት እነዚህ መገናኛ ብዙሀን ያደረጉት ድጋፍ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር እንደሚያወጣ የተነገረ ሲሆን ለተፈናቃዮቹ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በድጋፉ ተካተዋል ተብሏል።በዚህ መሰረት በአማራ እና በአፋር ክልል ላሉት ተፈናቃዮች የሚውሉ 250 ኩንታል የስንዴ ዱቄት 2 ሺህ 400 ባለ አንድ ሊትር ዘይት እንዲሁም 1ሺህ ብርድ ልብስ እና 400 ፍራሽን ያካተተ ነው።በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አስተባባሪነት ድጋፉን ያስረከበው የብሮድካስት ዘርፍ ምክር ቤት በቀጣይም እነዚሁ መገናኛ ብዙሀን ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአየር ሰዓት ለዚሁ የሰብዓዊ ድጋፍ ተግባር እንደሚያውሉ አስታውቋል።እነዚህ የሚዲያ ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት በተናጠል የየራሳቸውን ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያነሳው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ለተደረገው ድጋፍ አመስግኖ በቀጣይም ተጨማሪ ድጋፎች እንዲደረጉ ለህብረተሰቡ ጥሪ አቅርቧል።ጣቢያችን አቢኤስ ቴሌቭዥንም የዚሁ ድጋፍ አካል ሆኗል።ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram: https://t.me/ebstvworldwideFollow us on: https://linktr.ee/ebstelevision#ኢቢኤስ#EBS

5151