ገበናችን በውጭ ሚዲያዎች!
አለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ህፃን ሄቭን ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ የመደፈር፣ ታንቆ መገደል እና አስክሬኗ ተጥሎ መገኘት እየዘገቡት ይገኛል።
በጉዳዩ ዙሪያ ቢቢሲ የዜና ምንጭ ዘርዝር ያለ መረጃ ይዞ ወጥቷል። ቢቢሲ መረጃውን ማቅረብ ሲጀምር ዜናውን ሰቅጣጭ ነው ሲል ለአንባቢዎቹ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ነው ታሪኩን ማቅረብ የሚጀምረው።
ታዳጊ ህፃን ሄቭን ስለደረሰባት የግፍ ወንጀል የሚያትተው መረጃው ወላጅ እናቷም ስላጋጠማት የደህንነት ስጋት ጨምሮ አቅርቦታል።
የታዳጊ ሄቨን እናት እና አባት ከጥቂት ዓመታት በፊት ተለያይተው ወላጅ እናት ልጇን ለብቻዋ ታሳድግ እንደነበር የተናገረው ዘገባው እናት ሕይወቷ መመሳቀሉን ተናግሯል።