ጥራታቸውን ያልጠበቁ 112 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 500 ካርቶን የልብስ ሳሙናዎች መወገዳቸውን ፖሊስ ገለጸ::
ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በኤግዚቢትነት ተይዘው የነበሩ ጥራታቸውን ያልጠበቁና በህገ ወጥ መንገድ የተዘጋጁ የዋጋ ግምታቸው ከ112 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ 500 ካርቶን የልብስ ሳሙናዎች መወገዳቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳወቀ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከ4 ሺህ 1መቶ በላይ የሺሻ እቃዎች እና 40 ኪሎ ግራም ካናቢስ የተባለ አደዛዥ እጽ መወገዱንም ነው ፖሊስ የገለጸው፡፡
የማስወገድ ሂደቱ የተከናወነው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ላፍቶ መድኃኒያለም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑም ተነግሯል፡፡
ፖሊስ በኤግዚብትነት ይዞ ያስወገዳቸው ህብረተሰቡን የሚጎዱ፣ ለሠላም እና ጸጥታው ስጋት የሆኑ ነገሮች መሆናቸውን የተገለጸ ሲሆን የጤና ችግር የሚያስከትሉና ወንጀልን ለመፈጸም አነሳሽ የሆኑ ነገሮች ናቸው ተብሏል፡፡
በክፍለ ከተማው ለሠላምና ፀጥታ ስራ እንዲሁም ደህንነት ስጋት የሆኑ ጉዳዮች በጥናት ተለይተው ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የገለጸው ፓሊስ ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ ውጤታማ ስለማይሆን ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
