የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ በተጀመረው የበጀት ዓመት ከ1 ትሪሊየን ብር በላይ ብድር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
ባንኩ ይሄን ያለው የተጠናቀቀውን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻፀም አስመልክቶ ትናንት በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ የዲጂታል የብድር አማራጮችን ጨምሮ የተበዳሪዎችን ቁጥር ከ1.17 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ተችሏል ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት ሰጥቶ ከነበረው የብድር መጠን 68.7 በመቶ በመጨመር ከአንድ ትሪሊየን ብር በላይ ብድር በአዲሱ በጀት ዓመት ማዘጋጀቱን ገልጸው ህብረተሰቡ የብድሩ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
