ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ሽልማት ተበርከተላቸዉ።

በየዓመቱ እ.ኤ.አ ጁላይ 31 የሚከበረውን የፓን አፍሪካን የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ የሴቶች ቤተሰብ እና ሕፃናት ሚኒስቴር ለፕሬዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ሽልማት አበርክቷል። በተለያዩ የሙያ መስኮች በሀገር ውስጥ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን ለማብቃትም ሆነ በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሽልማቱ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።ሽልማቱን በዲሞክራቲክ ኮንጐ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ከወይንሸት ታደሰ መቀበላቸው ተነግሯል። በፕሮግራሙም ላይ ለሀገራቸው እና ለአህጉራቸው አፍሪካ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ታዋቂ አፍሪካዊያን ሴቶች ሽልማት መሰጠቱ ተገልጿል።