LatestNews

ሳፋሪኮም በዘርፉ ለሚያደርገው የመዋለ ንዋይ ፍሰት የሚያግዘውን ልዩ ብድር ከአሜሪካ መንግስት አገኘ፡፡

በኢትዮጵያ በቴሌኮም መስክ ሰፊ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ የመጣው ሳፋሪኮም የተሰኘው ድርጅት በዘርፉ ለሚያደርገው የመዋለ ንዋይ ፍሰት የሚያግዘውን ልዩ ብድር ከአሜሪካ መንግስት አገኘ፡፡ይህ የአሜሪካ መንግስት ለኩባንያው የሰጠው ብድር አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ተከትሎ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ካቆመ ወዲህ የተደረገ ሲሆን በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ የሚሰማራው ሳፋሪኮምን ጨምሮ ሌሎችም ኩባንያዎች በጥምረት ለሚሰሩት ስራ የሚረዳ የ500 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስለመሆኑ ታውቋል፡፡በኢትዮጵያ በቴሌኮም መስክ ቮዳፎምና ቮዳኮም ከተሰኙት ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር መዋለንዋዩን ፈሰስ ለማድረግ የመጣው ሳፋሪኮም የአሜሪካ መንግስት በቴሌኮም ዘርፍ ለማከናውነው ስራ የሚረዳ ብድር ማጽደቁ ትልቅ እርምጃና በመላው አፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ በጥምረቱ አማካኝነት ለምናደርገው የመዋዕለንዋይ ፍሰት ድጋፍም ነው ሲሉ የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፒተር ኒጋዋ ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ሳፋሪኮምን ጨምሮ ጥምረቱ 8 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለን ንዋይን ፈሰስ እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል፡፡ መረጃውን ከቢዝነስ ዴይሊ ያገኘነው ነው፡፡