LatestNews

በምርጫ የመንግስትነት ስልጣን የመረከብ እድሉን ካገኘ የብሔር ፌዴራሊዝምን ለመቀየር እንደሚሰራ ኢዜማ ተናግሯል

በምርጫ የመንግስትነት ስልጣን የመረከብ እድሉን ካገኘ የብሔር ፌዴራሊዝምን የኢትዮጵያዊያንን አብሮነት በሚያሳድግ ፌዴራላዊ ስርዓት ለመተካት እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ በፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኩል ተናግሯል ።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህን የተናገሩት ፓርቲው የቃል ኪዳን ሰነዱን ለሕዝብ ይፋ ባደረገበት መርሃ ግብር ላይ ሲሆን ፓርቲው ይፋ ያደረገው የቃል ኪዳን ሰነድ በምርጫ ተወዳድሮ የመንግስትን ስልጣን ከተረከበ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገባውን ቃል ያሰፈረበት ሰነድ መሆኑ ተሰምቷል፡፡የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ዘላቂ እድገትና አስተማማኝ ሠላም መፍጠር የሚያስችል የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት ከብሄር ፖለቲካ መውጣት ይገባል ባሉበት በዚሁ ንግግራቸው በኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታትና አሁንም ዜጎች በማንነታቸው ጥቃት ሲደርስባቸው የነበረው ብሄርን መሰረት አድርጎ በፀደቀው ሕገ መንግስት ምክንያት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ መንግስት ሕግ ሲያወጣ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እንጂ ለተወሰኑ ብሄሮች ወይም የሃይማኖት ተከታዮች ብሎ እንዳልሆነ የተናገሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ይህ ባለመሆኑ አገሪቷ ወደ ትርምስ ገብታለች ሲሉ ገልፀዋል፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs