LatestNews

ኬኒያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሶማልያ ስደተኞች የተጠለሉባቸውን ሁለት ጣቢያዎች እንደምትዘጋ አስታወቀች

ኬኒያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሶማልያ ስደተኞች የተጠለሉባቸውን ሁለት ጣቢያዎች እንደምትዘጋ አስታወቀች፡፡የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር የመጠለያ ጣቢያዎቹን የሚዘጋባቸውን ዝርዝር እቅዶች በሁለት ሳምንታት እድሜ ሊያቀርብ ይገባል፡፡ኬንያ የምትዘጋቸው ሁለቱ ግዙፍ መጠለያ ጣቢያዎች የዳዳብና የካኩማ መጠለያ ጣቢያዎች ሲሆኑ እነዚህ የሰሜን ኬንያ መጠለያ ጣቢያዎች በድምሩ 4 መቶ 10 ሺህ ስደተኞችን አስጠልለው ቆይተዋል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ኬንያ ቀደም ብላም የዳዳብ መጠለያን ለመዝጋት ስታቅድ የቆየችውም ጣቢያው ለሶማሊያ ድንበር ቅርብ በመሆኑ ለጸጥታዬ እሰጋለሁ በሚል ነው፡፡ የኬንያው የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፍሬድ ማቲያንጊ እንደሚሉት ከዚህ በኋላ ምንም ንግግር አያስፈልግም፤ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋምን የ14 ቀናት የዝግጅት ጊዜ ሰጥተነዋል ብለዋል፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs