InternationalNews

በአሜሪካ በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ከሚገኝ አየር ኃይል ሰፈር የተነሳ ቢ 52 የተሰኘ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ብዙም ሳይጓዝ በደረሰበት የመከስከስ አደጋ በውስጡ የነበሩ 8 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።

ኔውክለር ቦምብ የሚሸከመው አውሮፕላኑ ለተለመደ ፍተሻ በሚል ከአየር ኃይሉ በረራ እንደጀመረ ብዙም ሳይቆይ መከስከሱ ሲነገር ለፍተሻ ስራው የመጡ ሁለት የቦይንግ ሰራተኞችና ሌሎች ስድስት ባለሙያዎች ህይወት በአደጋው መቀጠፉም ነው የተሰማው፡፡

አውሮፕላኑ በተከሰከበት ስፍራ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር እስከሚውል በአየር ኃይሉ የአየር በረራዎች ተቋርጦ ነበር የተባለ ሲሆን የአደጋው መንስኤም እየተጣራ ነው ተብሏል፡፡

በአሜሪካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሲቪልና የወታደራዊ አውሮፕላኖች አደጋ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የሚገልጸው ቢቢሲ የዚህኛው አውሮፕላን አደጋ ምክንያት ገና በመጣራት ላይ መሆኑን ዘግቧል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews