EthiopiaNews

በደ /አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት አዝማሚያ ስላለ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት አዝማሚያ ስላለ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

ኤምባሲው ይሄን ማሳሰቢያ የሰጠው በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለ እና ከመንግስት ጋር አስፈላጊውን ግንኙነት እያደረገ መሆኑን በገለፀበት መግለጫ ላይ ነው።

ኤምባሲው የደቡብ አፍሪካ መንግስት በስደተኞች ላይ የሃይል ጥቃቶች እንዳይደርሱ በሁሉም አካባቢዎች ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርግ ከዚህ ቀደም መግለፁን አስታውሶ በቀጣይ ቀናት የፀጥታ ማስከበር ተግባሩን ያጠናክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።

ኤምባሲው በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ ህገወጥ ድርጊት እና ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት ሁኔታዎች እንዳሉ የሚጠቁሙ አዝማሚያዎች መኖራቸውን ገልጾ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀሱ አሳስቧል።

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከየአካባቢያቸው የመንግስት አካላት እና የኮሚኒቲ አደረጃጀቶች ግንኙነት በማድረግ መረጃዎች እንዲለዋወጡ ኤምባሲው መክራል። መረጃው በደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews