ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 1 የአሜሪካ ዶላርን በአማካይ 158 ብር ሸጠ።
ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 158 ብር መሸጡን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ሊያካሄድ የነበረውና በቴክኒክ ጉዳይ የተሰረዘውን የ100 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን ይህም ጨረታ ባንኩ የዛሬ ወር ገደማ ካካሄደው የግማሽ ቢሊን ዶላር ጨረታ ውጤት የአንድ ብር ከ98 ሳንቲም ቅናሽ ያሳየ ነው፡፡
ባንኩ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዶት በነበረው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ ዶላር 159 ብር ከ98 ሳንቲም መሸጡ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው ጨረታ 16 ባንኮች ተሳትፈው 8ቱ ባንኮች ማሸነፋቸው የተገለጸ ሲሆን በባንኮች ከ230 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት መመዝገቡም ተጠቅሷል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
