News

አዲስ ነገር – ቀን የተቆረጠለት የሰላም ንግግር

በመንግስትና በሽብርተኝነት በተፈረጀው የህወሃት ቡድን መካከል ከ4 ቀናት በኃላ የሰላም ንግግር ሊደረግ ስለመሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡

መረጃውን ይፋ ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሲሆኑ ለድርድሩ ቀን መቆረጡን የሚገልፅ መረጃ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በኩል ለኢትዮጵያ መንግስት መድረሱንና መንግስትም ሙሉ ፈቃደኝነቱን ማሳየቱን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለውን ራስን የመከላከል እርምጃ ተከትሎ የሰላም ንግግሩን ሊያደናቅፉ የሚችሉ የውንጀላ መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑ እንዳሳሰባቸው የጠቆሙት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪው ይህም ቢሆን ግን መንግስት በተቆረጠው ቀን በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን የሚገልፅ ምላሽ መላኩን አሳውቀዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New