News

አዲስ ነገር – በሩሲያ የተካሄደውን አመፅ የመሩት ይቭጌኒ ፕሪጐዚኒ ቤላሩስ መግባታቸውን የአገሪቱ መንግስት አስታወቀ።

በሩሲያ የተካሄደውን አመፅ የመሩት የሩስያው የቅጥረኛ ወታደሮች ድርጅት ዋግነር መሪው ይቭጌኒ ፕሪጐዚኒ ቤላሩስ መግባታቸውን የአገሪቱ መንግስት አስታወቀ።
የቤላሩስ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የሩስያ የቅጥረኛ ወታደሮች ድርጅት መሪው ይቭጌኒ ፕሪጐዚኒ ቤላሩስ መዲና ሚንስክ መግባታቸውን ይፋ አድርገዋል ።
የሩሲያው የቅጥረኛ ወታደሮች ዋግነር የጦር አለቃው ይቭጌኒ ፕሪጐዚኒ የዛሬ 3 ቀናት በሩሲያ ያካሄዱትን አመፅ ተከትሎ የት እንዳሉ ሚስጥር ሆኖ ቆይቷል። ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጨምረውም የዋግነሩ የጦር መሪ ይቭጌኒ ፕሪጐዚኒ በቤላሩስ ጥገኝነት ተመቻችቶላቸዋል ብለዋል።
የቤላሩስ ፕ/ት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የዋግነር የጦር መሪው ይቭጌኒ አመፁን እንዲያቆሙ ፣በሩሲያ የተከፈተባቸው የአገር ክህደት ክስ እንዲቋረጥላቸው እና በቤላሩስ ጥገኝነት እንዲያገኙ ማደራደራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

🇺🇸#አሜሪካ
በአሜሪካ ከ 20 አመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡባዊ የአገሪቱ ሁለት ግዛቶች የወባ ወረርሽኝ መከሰቱ ተዘገበ ።
በአሜሪካ የፍሎሪዳ እና ቴክሳስ ግዛቶች ከ20 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከሰተው የወባ ወረርሽኝ በበሽታው የተያዙ 5 ሰዎች መገኘታቸውን ነው የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ያስታወቀው ።
የወባ ወረርሽኙ በተከሰተባቸው የአሜሪካ 2ቱ ግዛቶች ወረርሽኙ እንዳይዛመት በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት መደረጉን አልጀዚራ ዘግቧል።

🇸🇩#ሱዳን
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ አዛዥ ጄኔራል ሙሐመድ ሀምዳን ዳግሎ የኢድ አል አድሃ በዓል ምክንያት በማድረግ ለሁለት ቀናት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ማድረጋቸውን ይፋ አድረገዋል፡፡
የልዩ ሀይሉ አዛዥ ጄኔራል መሐመድ ሀምዳን ዳግሎ መላው የሱዳን ሕዝብ የኢድ አል አድሃ በአል እንዲያከብር ልዩ ኃይላቸው ለሁለት ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም ማወጁን ነው በቪዲዮ መልዕክታቸው ትናንት ይፋ ያደረጉት ::
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ አዛዥ ጄኔራል ሙሐመድ ሀምዳን ዳግሎ ሰራዊታቸው አንዳችም ጥቃት እንዳይፈፅም እና ባለበት ሆኖ እንዲቆይ መታዘዙን አስታውቀዋል።
የልዩ ሀይሉ አዛዡ በተናጥል ያወጅነው የተኩስ አቁም ህዝባችን የደረሰበትን የጦርነት ሰቆቃ እንዲገታ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል ::
የሱዳን ጦር አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታ አልቡርሃን ትናንት ለኢድ አል አድሃ በአል የራሳቸውን የተናጥል የተኩስ ማድረጋቸውን ቪኦኤ በዘገባው አስታውሷል ።