Others

አዲስ ነገር

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንታና በዳውሮ በሁለቱ ዞኖች መካከል የሚገኘውን የጨበራ ጩር ጩራ ብሔራዊ ፓርክን ይበልጥ በማልት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም በመንግስት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው የገበታ ለአገር ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የኮይሻ ገበታ ለአገር ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶች በዚሁ ፓርክ ሥር በመሰራት ላይ ናቸው ብለዋል።

ከሚሰሩ መሰረተ ልማቶች መካከል የእንግዳ ማረፊያና መዝናኛ ቦታዎች እንዲሁም ተንጠልጣይ መሻጋገሪያ ድልድዮችና ሌሎችም የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ሊያራዝሙ የሚችሉ የልማት ሥራዎች እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።

በተለይ በፓርኩ ላይ የሚገኙ ሐይቆችንና ወንዞችን ከማልማት ባሻገር ዝሆኖችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ዝርያ ያላቸው የዱር እንስሳትን በመጠበቅና በመንከባከብ የፓርኩን እምቅ የተፈጥሮ ሐብቶችን መጠቀም እንደሚያስፈለግ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ አስከትለውም ይህንኑ የጨበራ ጩር ጩራ ብሔራዊ ፓርክን ይበልጥ ከማልት ባሻገር ለቱሪስቶች በየጊዜው ማስተዋወቁ ሚናው የጎላ በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ልኡካን በሥፍራ ተገኘተው እንዲጎበኙትና መረጃውንም ለህዝብ እንዲያደርሱ ተደርጓል ብለዋል። ዘገባው የፍስሐ ደሳለኝ ነው ።