EthiopiaNews

የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድህን ፈንድ ወይም በእንግሊዘኛው አጠራር Ethiopian Deposit Insurance Fund በይፋ ተቋቁሞ ስራ ጀመረ

ፈንዱ ዋና አላማው በየትኛም ባንክና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ላሉ ተቀማጭ ገንዘቦች የመድህን ሽፋን ለመስጠትና ለገንዘብ አስቀማጮች ጥበቃ በማድረግ መሆኑ ተነግሯል ፡፡

ይህ የመድን ፈንድ አንድ የፋይናስ ተቋም በተለያየ ምክንያት ሲከስር ወይም ሲወድቅ ዝቅተኛ ተቀማጭ ያላቸውን አስቀማጮች ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ እንዲሁም የሌሎችን በከፊል የሚመልስ አካል ነው።
ይህ የገንዘብ መድን ፈንድ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የተቋቋመ ሲሆን ተጠሪነቱም ለብሄራዊ ባንክ እንደሆነ ተነግሯል ፡፡
ፈንዱ የመድህን ሽፋን የሚሰጠው እስከ 100 ሺህ ብር ላለው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ይህ የሆነውም አሁን ባለው ሁኔታ 95 በመቶ የሚሆኑት አስቀማጮች በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ ያለው ተቀማጭ ገንዘብ ከመቶ ሺህ ብር በታች በመሆኑ ነው ተብሏል::

የፈንዱ አባል የሆኑ የፋይናንስ ተቋማት በሙሉ በዓመቱ ከያዙት ወይም ካላቸው አማካይ ተቀማጭ ገንዘብ 0 ነጥብ 3 በመቶ ዓረቦን መክፈል አለባቸው ::

በተያዘው በጀት ዓመት 6 ቢሊዮን ብር አረቦን ለመሰብሰብ መታቀዱንና በሩብ ዓመቱም በፈንዱ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ሰምተናል።

ለኢቢኤስ ዘገባ – ሐና አብዳታ