News

አዲስ ነገር – አሜሪካ ስለ ሰሜኑ ግጭት

አሜሪካ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በሰላማዊ መንገድ በሚፈታበት ሁኔታ ላይ ከአፍሪካ ህብረትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በኒውዮርክ ምክክር እንደምታደርግ ተነግሯል፡፡በአፍሪካ ህብረት ይመራል የተባለው የሰላም ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ በአጋርነት እየሰራች መሆኗን የጠቆመቸው አሜሪካ የኒውዮርኩ ውይይት የሚደረገው የኢትዮጵያ መንግስትና በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን ተማምነው በጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጥ የሚችሉበትን መንገድ ለመፍጠር ነው ብላለች፡፡አሜሪካ ይህንን ያለችው በቅርቡ ኢትዮጵያን ጎብኝተው በተመለሱት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛው ማይክ ሃመር በኩል ሲሆን ልዩ መልእክተኛው ከቃል ባለፈ ወደመሬት የወረደ ሰላም የማስፈን ተግባር ባይታይም ዲፕሎማሲያዊ መሳሪያዎቻችንን ሁሉ በመጠቀም ችግሩ በንግግር እንዲፈታ የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New