News

አዲስ ነገር – የኢትዮጵያ እና ሕንድ ግንኙነት

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ደመቀ መኮንን ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተመካከሩ፡፡

ምክክሩ በትምህርትና በንግድ ዘርፍ ላይ ሁለቱ አገራት ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ነው ተብሏል።ሁለቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ይህንን ምክክር ያደረጉት 77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በሚካሄድበት በኒውዩርክ ከተማ ነው።በቆይታቸውም ከትምህርትና ንግድ ጉዳዮች ባሻገር ስለኢትጵያ ወቅታዊ ሁኔታም መነጋገራቸው ተሰምቷል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New