News

አዲስ ነገር – አዲሱ የሩሲያ ዓለም

ሩሲያ የሀገሪቱን ቋንቋ ለሚናገሩ የውጭ ሀገር ማህበረሰቦች ድጋፍ እንድታደርግ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፓሊሲ ልታወጣ መሆኑ ተነግርዋል

ራሽያን ወርልድ ወይም “የሩሲያ አለም” በተባለው የሞስኮ የውጭ ፖሊሲ ሩሲያ የሀገሪቱን ቋንቋ ለሚናገሩ የውጭ ሀገር ማህበረሰቦች ድጋፍ እንድታደርግ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፓሊሲ ልታወጣ መሆኑ ተነግርዋል፡፡ ባለ 31 ገጹና “ሰብአዊ ፖሊሲ” ሲሉ የክሬምሊን ባለስልጣናት የጠሩት የውጭ ፖሊሲ ከዩክሬን ጦርነት መጀመር ስድስት ወራት በፊት የተፃፈ ሲሆን ሀገሪቱ “የሩሲያ አለም” የሚባለውን አስተሳሰብ በተገቢው ልትጠብቀው ይገባል ይላል፡፡ጽንስ ሀሳቡ በወግ አጥባቂ ሩሲያውያን አሳቢዎች የተረቀቀና የሞስኮ ወደ ጎረቤት ሀገሮች መስፋፋት ተገቢነትን ለማስረዳት የተጠነሰሰ ነው ሲሉ ምዕራባዊያን የዜና ምንጮች ተቀባብለው እየዘገቡት ነው፡፡እንደ አዲሱ የውጭ ፖሊሲ ከሆነ የሩሲያ ፌዴሬሽን መንግስት በውጭ ለሚኖሩ ዜጎቹም ተገቢውን ድጋፍና ጥበቃ ያደርጋል፡፡ሶቭየት ህብረት በፈረንጆቹ 1991 ከፈረሰች በኋላ ፕሬዝዳንት ፑቲን በተገንጣይ ሪፐብሊኮች ያሉ 25 ሚሊዮን ሩሲያዊያን እጣ ፈንታ ያሳስበናል ሲሉም ቆይተዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New