News

አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

#ሩሲያ

ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያ ቁሳቁሶችን መሸመት መጀመሯ ተሰምቷል ::ሸመታውን የጀመረችው ምዕራባዊያን አገራት ማዕቀብ መጣላቸውን ተከትሎ የጦር መሳሪያ እጥረት ስለገጠማት ነው ተብሏል።ሞስኮ በቢሊየን ዶላር እያወጣች በስፋት የጦር መሳሪያዎችን መሸመት መቀጠሏን አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣንን ዋቢ አድርጐ ቢቢሲ ዘግቧል ::

#ቻይና

በቻይና በደረሰ ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 65 ደረሰ:።በቻይና የደቡብ ምዕራብ ግዛት ሲቹዋን ትናንት በደረሰው የርዕደ መሬት ለህልፈት ከተዳረጉ ሰዎች በተጨማሪ 2 መቶ 48 የሚሆኑ ዜጐች የከፋ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል።በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 6 ሆኖ በተመዘገበው በዚሁ የመሬት መንቀጥቀጥ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

#ብሪታንያ

የብሪታንያ አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት እንዲያንሰራራ ለማድረግ ቃል ገቡ።በአገሪቱ ታሪክ 3ኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ስልጣን የተረከቡት ሊዝ ትረስ የግብር ክፍያ ላይ ማሻሻያ በማድረግ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት መልሶ እንዲያንሰራራ ትኩረት ሰጥቼ እሰራለሁ ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ በዛሬው እለት አዲሱ ካቢኔአቸውን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሲኤን ኤን ዘግቧል።

#ዚምባቡዌ

በዚምባቡዌ በተከሰተ የኩፍኝ በሽታ የሞቱ ህጻናት ቁጥር 698 መድረሱን ተሰምቷል። የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአገሪቱ በተከሰተው የኩፍኝ በሽታ እስካሁን 700 ገደማ ህፃናት ሲሞቱ 6ሺ 300 የሚጠጉ ህጻናት በበሽታው ተይዘዋል።በአጠቃላይ በአገሪቱ በኩፍኝ በሽታ ከተያዙት ግማሽ የሚያህሉት ከምስራቃዊ የማስሆናላንድ ግዛት መሆናቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New