አዲስ ነገር – ኢኮኖሚና አለም አቀፍ ጫና
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን በዘላቂነት የሚቋቋም ኢኮኖሚ ይኖራት ዘንድ አገራዊ አምራችነትን ማሻሻልና ተወዳዳሪ ምርቶችን ማምረት ልዩ ትኩረት ሊቸረው ይገባል ተብሏል፡፡
ይህ የተባለው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሚዘጋጀው የአዲስ ወግ የውይይት መድረክ አገራዊ አምራችነት በሚል ርዕስ በተካሄደበት ወቅት ሲሆን በውይይቱ የተካፈሉ ምሁራንም በዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታ የሚፈተነውን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመቋቋም በተለይ ተቋማት አምራችነትና ተወዳዳሪነት ላይ ትኩረት ያደረገ የሥራ ባህል መገንባት አለባቸው ብለዋል።
በሥራ ባህል ላይ ያለው የልቦና ውቅርም ሊሻሻል እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን በዚህም የዓለምን ተለዋዋጭ ተጽዕኖ መቋቋም የሚችል ኢኮኖሚ መገንባት እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡
በዓለም ላይ ጠንካራ ኢኮኖሚ የገነቡ አገራት ተሞክሮም አምራችነትን ማሻሻል ለመንግስት ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ዜጎች ጉዳይ መሆኑን እንደሚያሳይና ከዚህ ተሞክሮ በመነሳት ኢትዮጵያዊያን በትብብር አምራች የሆነ የሥራ ባህል መገንባት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡ መረጃውን ያገኘነው ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New