News

አዲስ ነገር – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሌላው ትልቅ ሆቴል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሌላው ትልቅ ሆቴል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መክፈቱን አስታውቋል፡፡
የሆቴሉ መከፈት የቦሌ ኤርፖርትን ዋና የመዳረሻ ማዕከል አድርገው ለሚንቀሳቀሱ መንገደኞች እና ሌሎች አየር መንገዶች ምቾት እንደሚፈጥር የጠቀሰው አየር መንገዱ ሆቴሉ ከመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ሁለት ጋር የተገናኘና ለመሳፈሪያ በሮችም ቅርብ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ስካይላይት በተባለው ሆቴል ስር ይተዳደራል የተባለው ይኸው ሆቴል ግንባታው ግንባታው ከሁለት አመታት በላይ የፈጀ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በመጀመሪያው ምእራፍ 41 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ተጠናቀው ዝግጁ መሆናቸውንና በአጠቃላይ 97 የመኝታ ክፍሎችን እንዳካተተ ከአየር መንገዱ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክተናል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New