News

አዲስ ነገር – የኬያው ፕሬዘዳንት በኢትዮጵያ

የኬያው ፕሬዘዳንት ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኘተው ለፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ፕሬዝዳንት ሩቶ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የስራ ቆይታ የሁለቱን ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።ፕሬዝዳንት ዊሊያም ጉብኝታቸውን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ በተለይ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለጋራ ብልጽግናችን የሚያግዙ ውይይቶችን እናደርጋለን ብለዋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New