News

አዲስ ነገር – ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ

ሳፋሪኮም የተባለው የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ዙሪያ በሚገኙ አስር ከተሞች የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን ያካሄደው ሳፋሪኮም ዛሬ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።የአዲስ አበባ 07 ኔትወርክ ደንበኞች የ4G ዳታ፣ የድምፅ ጥሪ እና የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።ደንበኞች 700 ላይ በመደወል የሳፋሪኮም የጥሪ ማዕከልን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ አገልግሎቶቹም በ5 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሱማሊኛ፣ ትግሪኛ እና እንግሊዝኛ የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New