News

አዲስ ነገር – የገንዘብ ተቋማቱ ጉባኤ

ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ 70 ሚሊየን ተጨማሪ ሰዎች ወደ ድህነት መግባታቸውና መካከለኛ ገቢ የነበራቸው ሰዎች ደግሞ በ4 ከመቶ ቅናሽ ማሳታቸውን ተከትሎ የብዙ አገራት ድጋፍ ፍላጎት ከፍ ማለቱ እንደማይቀር ተገምቷል።የአለም ባንክ ከታዳጊ አገራት ጋር አብሮ በመስራት ኢኮኖሚያዊ እድገታቸውን የመደገፍ ስራ የሚሰራ ተቋም ሲሆን አለም አቀፉ የገንዘብ ተቆጣጣሪ አካል የሆነው ኢንተርናሽናል ሞኒተሪ ፈንድ ደግሞ አለማችን ላይ ያለው የገንዘብ ፍሰት የተረጋጋ እንዲሆን የሚሰራ ተቋም ስለመሆኑ ይነገራል።በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በነዚሁ ተቋማት አመታዊ ስብሰባ ላይ ለመታደም ዋሽንግተን ዲሲ ስለ መድረሱ ተነግሯል፡፡ቡድኑ የመጀመሪያ የቡድን ውይይቱን አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማካሄዱም ተነግሯል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New