News

አዲስ ነገር – የዩክሬን ስንዴ

የዩክሬን የስንዴ ምርት በጥቁር ባሕር በኩል ወደ ተለያዩ የአለማችን ሃገራት እንዲሰራጭ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ ሌሎች 4 ሃገራት 206 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ስለመሰራጭቱ ተሰምቷል፡፡

ይህን የተናገረው የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስ ኤይድ ድጋፉ ወደ ኬንያ ኢትዮጵያ እንዲሁም የመንና ሶማሊያ መጓጓዙን በመጠቆም ሱዳንም ስንዴውን ካገኙ አገራት መካከል እንደምትገኝ ገልጿል፡፡ የዩክሬንና ሩሲያ ጦርነትን ተከትሎ ዋና የወጪ ንግድ መስመር የነበረው ጥቁር ባህር ለረጅም ጊዜ መዘጋቱ የአለም የምግብ ዋጋ እንዲንር ምክንያት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ሩሲያና ዩክሬን በተባበሩት መንግስታት ድርጅትና በቱርክ አሸማጋይነት ማስተላለፊያ መስመሩ እንዲከፈት የተስማሙት ባሳለፍነው ሃምሌ ወር ላይ ነበር፡፡ይህንን ስምምነታቸውን ተከትሎም በመስከረም ወር 13 ቀናት ብቻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን ስንዴ ከዩክሬን የወጣ መውጣት የቻለ ቢሆንም ቁጥሩ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የ34 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ነው ተብሏል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New