News

አዲስ ነገር – ዳንጎቴ ከአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሃብት መባላቸው እና ሌሎችም መረጃዎች

🇨🇳#ቻይና
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ አሜሪካ የቻይና እድገት እንዲገታ ፅኑ ፍላጐት አላት ሲሉ ወቀሷት።
ፕሬዚዳንቱ በአሜሪካ የሚዘወረው ምዕራቡ ዓለም ቻይናን ማረቅ አለፍ ሲልም መክበብ እና ከተቻለም የቻይናን እድገት ማስቀረት ይፈልጋል ሲሉ ለአገሪቱ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል ።
“ይሄው የአሜሪካ እና ተባባሪዎቿ ቻይናን የመድፈቅ ስትራቴጂ የሀገራችንን ልማት ለማረጋገጥ ግዙፍ ጋሬጣ ሆኖብናልክ” ብለዋል ሺ ጂን ፒንግ፡፡
አሜሪካ በህግ የሚመራውን የዓለም አቀፍ ስርአት እንዲዳከም ቻይና እየሰራች ነው ስትል ብርቱ ክስ እያቀረበች መሆኑን አር ቲ በዘገባዉ አስታውሷል ።
#የመንግስታቱ ድርጅት
የመንግስታቱ ድርጅት የህፃናት መርጃ ተቋም “ዩኒሴፍ ” በ12 አገራት ያሉ ነፍሰጡር እናቶች ለከፋ ያልተመጣጠነ የምግብ እጥረት ችግሮች መዳረጋቸውን አስታወቀ።
ዩኒሴፍ አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ የዩክሬን ጦርነት ባስከተለው የምግብ ዋጋ ንረት ሳቢያ በ12 አገራት ላልተመጣጠነ የምግብ እጥረት ችግሮች የተዳረጉ ነፍሰጡር እናቶች ቁጥር በ2 አመታት ውስጥ በ25 ከመቶ ማደጉን አስታውቋል ።
ለከፋ ያልተመጣጠነ የምግብ እጥረት ከተዳረጉት ነፍሰጡር እናቶች ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ አስሩ የአፍሪካ አገራት ሲሆኑ ቀሪዎቹ 2 አገራት ከእስያ መሆናቸውን ተቋሙ ጠቅሷል።
በመላው ዓለም እድሜአቸው ከ2 አመት በታች የሆኑ 51 ሚሊየን ህጻናት ከተመጣጠነ የምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ መቀንጨራቸውን ኤፒ ዘግቧል ።
🇹🇳#ቱኒዚያ
የዓለም ባንክ፣ የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ስደተኞችን አስመልክቶ ሰጡት የተባለው “ዘረኛ ንግግር”ን ተከትሎ ለአገሪቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አቋርጧል።
ባንኩ የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ ስደተኞችን የሚያንቋሽሽ ንግግር ማድረጋቸው በጭራሽ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ከአገሪቱ ጋር የምናደርገውን የበጀት ድጋፍ ንግግር አቋርጠናል ብሏል-በመግለጫው።
ተሰናባቹ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ ቱኒዚያ ከባንኩ የድጋፍ ማዕቀፍ እንድትወጣ እና የባንኩ አስተዳደር ከአገሪቱ ጋር የሚያካሂደውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ በቱኒዚያ እየተስፋፋ ለመጣው ወንጀል ስደተኞች ተጠያቂዎች ናቸው በሚል የሰጡት የዘረኝነት አስተያየት በተለይ ስደተኞች ላላስፈላጊ ጥቃት እንዲዳረጉ ምክንያት መሆኑን ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል።
🇳🇬#ናይጄሪያ
ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ከአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሃብት መሆናቸው ተነገረ።
የወቅቱን የቢሊየነሮች ደረጃ በየጊዜው ይፋ የሚያደርገው ብሉምበርግ ሚዲያ፤ ናይጄሪያዊው ባለሀብት ዳንጎቴ ለ12ኛ ተከታታይ አመታት የአፍሪካ ቁጥር 1 ባለሃብት አድርጎ ሲመርጣቸው የቢሊየነሩ ሃብት 19.4 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቋል ።
የደቡብ አፍሪካው ባለፀጋ ጆሃን ሩፐርት 12.1 ቢሊዮን ዶላር በማፍራት ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ቱጃር መሆናቸውን አር ቲ ዘግቧል።
የብሉምበርግ ሚዲያ ምርጥ 5 መቶ ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ከአፍሪካ 19 ቢሊየነሮች መካተታቸው በዘገባው ተመልክቷል ።

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New