አዲስ የፋይናንስ ህግ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢንዱስትሪው ሊያገኝ የሚገባውን የብድር ድርሻ እንዲያጣ ያደረጉ ሰው ሰራሽ ችግሮችን የሚቀርፍ ህግ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ትናንት በተካሄደው የ4ኛው ዙር ” የኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚያቀርቡት ብድር አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ሃብት ምን ያህል ፐርሰንቱ ወደ ኢንዱስትሪ መፍሰስ እንዳለበት የሚወስን በግልም በመንግስትም ባንክ አዲስ ህግ እንደሚወጣ ጠቅሰው ይህ ውሳኔ ዘርፉ ለሚገጥመው የገንዘብ እጥረት ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ በውጭ ምንዛሬ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 14.5 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏን ተናግረዋል።
መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይፋዊ የማህበራዊ ገፅ የተገኘ ነው፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
