LatestNewsSports

አጫጭር የኢቢኤስ ስፖርት መረጃዎች

– በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡክ በዛሬው እለት በቦሌ አለም አቀፍ ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።- በቶኪዮ ኦሎምፒክ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ 5 ሺ ሜትር የመወዳደር ፍላጎት እንደነበረው ተናግሯል። በአቀባበሉ ላይም ከጋዜጠኞቹ ጋር ቆይታ ያደረገው አትሌቱ በአመራሮቹ ላይ የነበረው አለመግብባት አትሌቶቹ ላይ ተጸኖ መፍጠሩንም ተናግሯል አትሌቱ በመኖርያ አከባቢው ሲደርስም ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።- የቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ አዲሱ አሰልጣኝ ዝላትኮ ክራምፖቲች በመጭው ቅዳሜ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ክለቡ በፌስ ቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል።- አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከፒ ኤስ ጂ ጋር የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን የማሸነፍ ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል።- የሮማው ጄነራል ማናጀር ቲያጎ ፒንቶ የቴሚ አብርሃምን ዝውውር ለማጠናቀቅ ለንደን መድረሳቸው ተሰምቷል።- የቀድሞው የአትሌቲኮና የቼልሲ ተጨዋች የነበረው ዲያጎ ኮስታ ወደ ብራዚሉ ክለብ አትሌቲኮ ሚኔሮ ለማምራት በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ተዘግቧል።- የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በታሪኩ ለ2ኛ ጊዜ የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን የግሉ አድርጓል።- የማንችስተር ሲቲው የኳስ አቀጣጣይ ፊል ፎደን ለ 4 ሳምንታት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተነግሯል።