EthiopiaNews

ኢሰመጉ ስለምርጫው

🔸ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ራሱን አሸናፊ ከማድረግ እንዲቆጠብ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)አሳሰበ።

🔸ጉባኤው ባወጣው የምርጫ መታዘብ ቅድመ መግለጫ፣ በተለይም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አንቂዎችና ተጠቃሚዎች የእጩ ተወዳዳሪዎችን ጊዜያዊ ውጤት በማጋራት ማኅበረሰቡን ከማደናገር እንዲታቀቡ ጥሪ አቅርቧል።

🔸ኢሰመጉ በዋናው ጽሕፈት ቤቱ ባደራጀው የኹነቶች መቆጣጠሪያ ክፍልና ባሰማራቸው 433 ቋሚና ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎች አማካኝነት ከ800 በላይ የምርጫ ጣቢያዎችን መታዘቡን ገልጿል።

🔸ድርጅቱ ባካሄደው ክትትል በድምፅ መስጫው ዕለት በርካታ ተግዳሮቶች መስተዋላቸውን የጠቀሰ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል አዲሱ የዲጂታል የመራጮችና የእጩዎች ምዝገባ ሥልት መጀመሩ የሚበረታታ ቢሆንም የአስፈጻሚዎች ሥልጠና ማነስ ለመራጮች መጨናነቅና ለሰዓት መራዘም ምክንያት መሆኑን አልሸሸገም።

🔸ከዚሁ ጋር ተያይዞ በበርካታ አካባቢዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጥ፣ በጣቢያዎች የመራጮችን ስም የሚያጣራው ባለሙያና መዝገብ አንድ ብቻ መሆን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባና በአካባቢው በቂ የሰልፍ አስተባባሪዎች ባለመኖራቸው መራጮች ለረዥም ሰዓታት ለእንግልት መዳረጋቸው በዋና ዋና ችግርነት አንስቷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews