EthiopiaLatestNews

ከተጠበቀው በታች ውጤት ያስመዘገበው የኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን በመጪው ረቡዕ ወደሀገር ይገባል፡፡

ከተጠበቀው በታች ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን በመጪው ረቡዕ ወደሀገር ይገባል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በውድድሩ ላይ በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሁለት የነሀስ ሜዳሊዎች ከዓለም 56ኛ ከአፍሪካ ደግሞ አምስተኛ ሆኖ ጨርሷል፡፡ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከኦሎምፒኩ መልስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ አሰልጣኝ ባምላክ በጃፓኑ የኦሎምፒክ ውድድር አምስት ያህል ጨዋታዎችን በተለያዩ የዳኝነት ሀላፊነቶች ላይ ሆኖ መርቷል፡፡ የቶኪዮ ኦሎምፒክ አስደናቂ አሀዞች ተመዝግበውበት ተጠናቋል፡፡ 19 ቢሊየን ፓውንድ ያህል ወጪ የተደረገበት ውድድሩ በኮሮና ምክንያት በእጅጉ ቢፈተንም አስደናቂ አጋጣሚዎችን አስመልክቶ በድምቀት ተጠናቋል፡፡ በዚህ ረገድም ኦሎምፒኩ 34 ሺህ እና 70 ሺህ ህዝብ ብቻ ያላቸው ትንንሾቹ ሀገራት ሳንማሪኖ እና ቤርሙዳ ጭምር ሜዳሊያዎችን ያሳኩበት ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የ 13 አመቷ ብሪታንያዊት የስኬት ቦርድ ተወዳዳሪ ስካይ ብራውን የብር ሜዳሊን ያገኘችበትም ነበር፡፡ በውድደሩ ላይ አምስት ያህል በፍ ቅር የተጣመሩ ጥንዶች መሳተፍም ውድደሩን ታሪካዊ አድርጎት አልፏል፡፡ ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገሯ ውጪ ብዙ ሜዳሊያዎችን ባስመዘገበችበት የጃፓኑ ኦሎምፒክ አሜሪካ በቀዳሚነት ጨርሳለች፡፡ ቻይናውያኑ በሚታወቁባቸው እንደ ጠረጴዛ ቴኒስ እና ክብደት ማንሳት አይነት ውድድሮች እንደተለመደው አስደናቂ ውጤቶችን ቢያስመዘግቡም በአሜሪካ ተበልጠው በሁለተኛነት ጨርሰዋል፡፡