News

ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የወጪ ንግድ 390 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተነገረ

ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች የወጪ ንግድ 390 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዚህም የዕቅዱን 87 በመቶ ማሳካት ቢቻልም ዘርፉ አሁንም የግብዓት ችግር፣ የመሰረተ ልማት እጥረት፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል ውስንነት፣ የፋይናንስና መሰል ችግሮች እንቅፋት እንደሆኑበት ተገልጿል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአምስት ክልሎች ብቻ 396 ኢንዱስትሪዎች በተጠቀሱትና መሰል ችግሮች ምክንያት ስራ አቁመዋል ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለችግሮቹ ዕልባት ሰጥቶ ወደ ስራ ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት ከሁሉም አይነት የወጭ ንግድ 2 ነጥብ አምስት ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማስታወቁን ከዥንዋ ዘገባ ላይ ተመልክተናል፡፡