Ethiopia

ክስ የተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች

ከኢትዮጵያ እስከ ሊቢያ በተዘረጋ ሰንሰለት በሰው ልጆች የመነገድ ወንጀል በተጠረጠሩ 11 ተከሳሾች ላይ ክስ መመስረቱን የፍትህ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

ተከሳሾቹ ከኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ኤርትራ ሰዎችን በመመልመል ወደ አዉሮፓ እናሻግራችኋለን በማለት በሀገወጥ መንገድ በማጓጓዝና በሊቢያ በረሃዎች በማገት ከ750 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ገንዘብ ሲቀበሉ ቆይተዋል ተብሏል፡፡

በዚህ ድርጊትም ከ2015 እስከ 2018 ዓ.ም ታህሳስ ወር ድረስ ብቻ 3ሺህ 887 ተበዳዮች ቤተሰቦች ከአራት ቢሊዮን ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰባቸዉ በክሱ ላይ ሰፈረ ሲሆን ከሳሾች የግል ተበዳዮችን በእዳ መያዣነት ይዘው ባቆዩበት ወቅት የ133 ተጎጂዎች ህይወት ማለፉ እንዲሁም 76 ሴት ተጎጂዎች ተገደዉ እንደተደፈሩ መረጋገጡ በክስ ዝርዝሩ ተካቷል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/