EthiopiaNews

ኸርት አታክ ኢትዮጵያ የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለ200 ሰዎች ነጻ የልብ ሕክምና ሊሰጥ ነው መሆኑን አስታወቀ።

ኸርት አታክ ኢትዮጵያ የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለሁለት መቶ ሰዎች ነጻ የልብ ሕክምና ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ።

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ መስራች እና ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኦብስኔት መርድ የፊታችን እሁድ ሰኔ 28 ለሁለት መቶ ኢትዮጵያውያን የነጻ የልብ ህክምና እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ሕክምናው ከአሜሪካ ፣ ብሪታንያ ፣ ካናዳ እና ህንድ በተውጣጡ 55 በጎፈቃደኛ ሀኪሞች እንደሚሰጥ ዶ/ር ኦብስኔት ገልፀዋል።

ኸርት አታክ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህ ቀደም ለ4 ግዜ ነፃ የልብ ህክምና መስጠቱ ይታወሳል። መረጃው ከኸርት አታክ ኢትዮጵያ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews