የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅንና የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡
ህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅንና የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባው የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ነው አዋጁን በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው፡፡
ከዓመታት ጥበቃ በኋላ በዛሬው ዕለት የጸደቀው አዋጁ ከመረጃ አሰጣጥ ጋር የተያያዙ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስራት የሚያስቀጡ የጥፋት አይነቶችን ያካተተ ሲሆን ከመንግሥት አካላት በተጨማሪ በግል ድርጅቶች ይዞታ ስር የሚገኝ መረጃን መጠየቅ የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በተመሳሳይ ምክር ቤቱ ላለፉት 25 አመታት አገልግሎት ላይ የነበረው የፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅን ሙሉ በሙሉ የሚተካና ለህዝበ ሙስሊሙ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል ያለውን አዲሱን የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
