የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በዓለማችን ከፍተኛ ተጓዦች ከተመረጡ የዩኔስኮ ምርጥ አምስት ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ተገለጸ፡፡
የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በዓለማችን ከፍተኛ ተጓዦች ከተመረጡ የዩኔስኮ ምርጥ አምስት ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ተገለጸ፡፡
ዩሮኒውስ አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት የዓለም ሀገራትን በመጎብኘት “ዩኤን ግራንድማስተር” የተባለውን ታዋቂ የክብር ማዕረግ ያገኙ አንጋፋ ተጓዦች ካስቀመጧቸው ተወዳጅ የዩኔስኮ የዓለም ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅርአብያተ ክርስቲያናት በምርጥ 5 ምርጫዎች ውስጥ መካተት ችሏል።
ተጓዦቹ እንደ አንኮር ዋት እና ታላቁ የቻይና ግንብ ካሉ ታዋቂ ቅርሶች ጎን ለጎን ስለ ላሊበላ ድንቅ የጥበብ ጥልቀትና መንፈሳዊ ግርማ ምስክርነታቸውን መስጠታቸው ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ሊታይ የሚገባው ቀዳሚ የጉዞ መዳረሻ መሆኑም ነው የተነገረው።
ይህንን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ይበልጥ ለማጎልበት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች በመጠበቅና በመንከባከብ በዘላቂ የቅርስ ልማትና ጥበቃ መርሆዎች መሰረት ለትውልድ ለማስተላለፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ደግሞ የቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
