EthiopiaLatestNews

የመንግስት ማሳሰቢያ!

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የሽብር ጥቃት ስጋት እንዳለ አድርገው የሚገልጹ የአለምአቀፉ ማህበረሰብ አባላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ መንግስት አሳስቧል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታው ከበደ ዴሲሳ ዛሬ ረፋድ ላይ በሰጡት መግለጫ በተለይም የአሜሪካ መንግስት ተቋማት እንዲሁም አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ከእውነታው የራቀ ስጋት ከመፍጠር ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን ብለዋል። ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ መግለጫቸው አክለውም ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ ከተሞች እየገለጹ የሚገኙት ድጋፍና ባለፉት ሶስት ወራት በህጋዊ መንገድ የላኩት ገንዘብ መጠን መጨመር ኢትዮጵያ ያለውጭ ድጋፍ እንደአገር መቀጠል እንደምትችል ያሳየ ነው ብለዋል።ከዚህ በተጨማሪ አስታራቂ በመምሰል በሽብርተኝነት ከተፈረጀው የህወሓት ቡድን ጋር አብረው የሚንቀሳቀሱ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አካላት ድርጊታቸው በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል።ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram:

https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

#ኢቢኤስ#EBS