EthiopiaNews

የምርጫው ጊዜያዊ ውጤት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን 825 የምርጫ ክልሎች ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ማድረጋቸውን ተናገሩ፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ይሄን ያሉት ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

ሰብሳቢዋ ቦርዱ ምርጫ ባካሄደባቸው አጠቃላይ 1 ሺህ 138 የምርጫ ክልሎች መካከል፣ 825ቱ የማዳመር ሥራቸውን ሙሉ በሙሉ አጠናቀው ጊዜያዊ ውጤቱን ይፋ እንዳደረጉ ገልፀዋል።

ሰብሳቢዋ የድምፅ ማዳመር ስራን በመስራት ላይ ያሉ ቀሪ የምርጫ ክልሎች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡