የሩስያና ዩክሬን ጦርነት መቀጠል
ሩሲያ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ድል በዓል ለማክበር እየተዘጋጀች ብትገኝም ከዩክሬን ጋር እያካሄደች የምትገኘው ጦርነት መቀጠሉ ተነገረ፡፡
ምንም እንኳን ሩሲያ እና ዩክሬን ዛሬ የበዓሉን ዋዜማ ጨምሮ የበዓሉን ዕለት ነገን የሚያካትት የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸውን ቢገልጹም ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን አጠናክረው መቀጠላቸው ነው የተነገረው፡፡
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሩሲያ በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳችውን ድል ለማክበር ሞስኮ ነገ ትልቅ ድግስ መደገሷ ቢነገርም አንዱ ሀገር ሌላኛውን ስምምነቱን በመጣስ እየከሰሰ ይገኛል ተብሏል፡፡
ዩክሬን በነገው ዕለት በሞስኮ በሚከበረው የድል በዓል ላይ የሚካሄደውን ወታደራዊ ትርዒት ለማስተጓጎል ከሞከረች የሀገሪቱ መዲና ኬይቭ እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የሚሳኤል ውርጅብኝ እንደሚጠብቃት ሩስታ ማስጠንቀቋም አይዘነጋም፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
