የሰብአዊ መብት ጥሰቶች
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ አካላት የሚፈጸሙ ከሕግ አግባብ ውጪ የኾኑ የአፈሳ እና የጅምላ እስር ድርጊቶች አሁንም አሳሳቢ ኾነው የቀጠሉ ችግሮች መሆናቸውን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ይሄን ያለው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ባከናወናቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትሎች የተለዩ ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው ውይይት ነው።
ኢሰመኮ በክልሉ በወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ የመብት ጥሠት በሚፈጽሙ የፖሊስ አባላት ላይ አሥተዳደራዊ ርምጃዎችን ያለመውሰድ፣ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎችን የማሠርና በሕግ በተቀመጠ ቀነ ገደብ ተጠርጣሪዎችን ፍርድ ቤት ያለማቅረብ ችግሮች እንደሚታዩ በሪፖርቱ ገልጿል።
ኮሚሽኑ ችግሮቹን ለማሻሻልና አጠቃላይ የተጠርጣሪዎች አያያዝ ሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ እንዲከናወን ባለድርሻ አካላት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል።
መረጃው ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
