የሳይበር ጥቃት
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከ50 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን ማክሸፍ መቻሉን አስታወቀ።
አስተዳደሩ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን በገመገመበት ወቅት ነው ይህንን ይፋ ያደረገው።
አስተዳደሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሀገሪቱ ተቋማት ላይ 50,155 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መሰንዘራቸውን ገልፆ ከእነዚህም መካከል ሰርጎ ገብ ጥቃቶች 20,601 ሙከራዎችን ወይም 41 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ ድርሻ በመያዝ ቀዳሚ ሆነዋል።
አስተዳደሩ በዘረጋው ስርአቱ ከጥቃቶቹ ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑትን ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ ተችሏል ተብሏል።
ከሙስና፣ ከማጭበርበር እና ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር የተያያዙ 5,604 የማጭበርበር መከላከል ስራዎችን በማከናወን በዜጎችና በተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረውን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውስ አስቀድሞ መከላከል መቻሉ ተገልጿል።
መረጃው ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
