EthiopiaNews

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 789 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስታወቀ።

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 49ኙ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

‎ሚኒስቴሩ መስከረም 5/ 2018 አ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ79 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለሳቸውን አሳውቋል።

‎ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል። መረጃው ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv