የቀድሞ ታጣቂዎች
የብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን በአማራ እና አፋር ክልሎች ከ1540 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በአማራ ክልል በጎንደር-ጠዳ ከ720 በላይ ፣ በኮምቦልቻ 520 እንዲሁም በአፋር በጉሊና 300 የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና አጠናቀው ወደ ማህበረሰቡ መመለሳቸውን ገልጿል።
በአማራ እና አፋር ክልሎች በተሃድሶ ሥልጠና የተሳተፉ 1540 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች የመልሶ ማቀላቀል ክፍያ ተከፍሏቸው ወደ ማሕበረሰቡ ተመልሰዋል ተብሏል።
ኮሚሽኑ ከህዳር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን በትግራይ፣ በአፋር፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ዘጠና ሺህ የሚሆኑ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉን ገልጿል። መረጃው ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
