የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ግኝት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3.6 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቱን አስታውቋል።
ባንኩ ይሄን ያስታወቀው የ2025/26 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ ላይ ነው።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 493 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ ማግኘቱን ገልፆ አጠቃላይ ተቀማጩን ባለፈው በጀት ዓመት መጨረሻ ከነበረበት 1.68 ትሪሊዮን ብር ወደ 2.1 ትሪሊዮን ብር በላይ ማሳደጉንም ገልጿል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በብድር ስርጭትና ፍትሀዊነት፣ በወጪ ቅነሳ፣ በደንበኞች ምልመላና አያያዝ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
መረጃው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
