EthiopiaNews

የብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የአስከሬን ሽኝት መርሃ ግብር

የ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።

በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የኢትዮጵያ ቅርስ በመሆኗ መሪዎቿን በሐዘን በምንሸኝበትም ወቅት ቢሆንም ዜማዋንና ትውፊቷን ለዓለም ለማስተዋወቅ ይረዳት ብለዋል ፤ እንዲሁም የአሁኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘሐነበረ ተክለ ሃይማኖት በመልእክታቸው ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ብዙ ሰርተው የዚችን ዓለም የመጨረሻ ዘመናቸውን ፍጻሜ በአርምሞ ጨርሰዋል ብለዋል።

ለአባታችን እረፍት ነው፤ እኛ ግን እስከምንጠራ ድረስ በሰላም አብረንና ተባብረን ይህንን ክፉ ጊዜ ለማለፍ መትጋት ይኖርብናል ሲሉ መልእክታቸው አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 4ኛ ፓርትርያርክ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ የሐዘንና የስንብት ፊርማቸውን አኑረዋል።

የብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን ከመስቀል አደባባይ የነበረው የስንብት መርሃ ግብር በመጠጠናቀቁ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመመለስ ላይ ነው።

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።
Telegram: https://t.me/ebstvworldwide
Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

ኢቢኤስ

EBS