EthiopiaNews

የተለቀቀው የፌደራል በጀት

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ታደሠ ወረደ የፌደራል መንግሥት ለክልሉ መልሶ ማቋቋሚያ፣ ለመንገድ ግንባታ፣ ለትምህርት ቤቶችና ለሌሎች የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚውል በጀት መልቀቅ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

የበጀት መስተጓጎል ሲስተዋል መቆየቱን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ለአንዳንድ አገልግሎቶች የሚውል በጀት መለቀቁንና ለክልሉ የመንግስት ሰራተኞች የሚውል በጀት ለማግኘት እየተጠባበቅን ነው ሲሉ መናገራቸውን የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ በመገኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር የመከሩት ፕሬዝዳንቱ በነበራቸው ውይይትም የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ የኢንቨስትመንት፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የመሠረተ ልማት፣ የመልሶ ማቋቋምና የተፈናቃዮች ጉዳይ እንዲሁም ነዳጅ፣ ባንክ፣ በጀትና የገንዘብ እጥረት ጉዳዮች መነሳታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/