EthiopiaNews

የተመድ ዋና ጸሃፊ በኢትዮጵያ

🔸በፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ መቀመጫ ማጣቷ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ።

🔸የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመሰረተበት 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ዝግጅት ላይ ለመታደም አዲስ አበባ የገቡት ዋና ጸሃፊው ይሄንን ያሉት የአፍሪካ ሕብረትና የተመድ 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

🔸ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ያነሱት ዋና ጸሃፊው ይህ ሊስተካከል ይገባል ነው ያሉት፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews