Others

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትላንት ከስዓት ባካሄደው ስብሰባ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ስለ ጉዳዩ መግለጫ ለማውጣት አቅዶ የነበረ ቢሆንም መግለጫ ሳያወጣ ቀርቷል።

ዶቼቬሌ እንግሊዘኛ ባወጣው ዘገባ እንደገለጸው ከሆነ የመንግስታቱ ድርጅት በበይነ መረብ ትላንት ባካሄደው ስብሰባ ላይ በፌደራልና በህውሀት ቡድን መካከል ስለተነሳው ጦርነት የተወያየ ሲሆን በጉዳዩ ላይ በአፍሪካና በአውሮፓ ተወካዮች መካከል ስለ ጉዳዩ መነሳት #የለበትም#አለበት በማለት ያለመግባባት መፈጠሩን ነው የዘገበው።
አለመግባባት ባስነሳው በዚህ የኢትዮጵያ ጉዳይ አፍሪካዊያኑ ተወካዮች ጉዳዩ በውስጥ የሚፈተና ነው ቢሉም እንደ ፈረንሳይ፣ ጀርመንና ቤልጂየም ያሉ ሀገራት ውይይቱ መካሄድ አለበት በማለት አለመስማማታቸውን ተገልጿል።
ምንጮቼ ነገሩኝ ያለው ዶቼቬሌ እንግሊዝኛ የደቡብ አፍሪካው ተወካይ ጉዳዩ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመራ ጊዜ ሊሰጠው ይገባል ያሉ ሲሆን አሁን የሚወጣው መግለጫ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን መግለጻቸውን አስታውቋል።
ስማቸው ያልተገለጸ የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማት በበኩላቸው በጦርነቱ ያላቸውብ ስጋት በመግለጽ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃትን በማውገዝ ለንጹሀን ሰዎች ከለላ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ነው የተገለጸው።
የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣዋ መረጃ በትግራይ ክልል የሚኖሩ ዜጎች ጉዳይ ያሳስበኛል ያለ ሲሆን እስካሁንም 39 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ወደ ሱዳን ማቅናታቸውን አስታውቋል። ከእነዚህም ስደተኞች መካከል 17 ሺህ የሚደርሱት ህጻናት መሆናቸውን ነው ያመለከተው።
በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ በሉዓላዊ አገር ላይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ እንዲከበር አጥብቃ ትሻለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እያካሄደችው ትገኛለች ያሉትን የህግ ማስከበር ዘመቻ በራሷ አቅም በህግ መሰረት ትፈታዋለች ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡
አገሪቱ በሉዓላዊ አገር ላይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ እንዲከበር አጥብቃ የምትሻ ረጅምና አኩሪ ታሪክ ያላት መሆኗን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሲመሰረት መስራች አባል አገር እንዲሁም የያኔው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ሲመረትም የላቀ ሚና የተጫወተች አገር መሆኗን አስታውሰዋል።
በዚህም መሰረት በመንግስታቱ ድርጅት ቻርተር አንቀጽ 2(7) እንደተቀመጠው የዓለም ዓቀፍ የህግ ስርዓት መሰረታዊ መርህ በሉዓላዊ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባትን እንደሚደነግግና የዓለም አቀፍ ፍርድ ሸንጎም በተደጋጋሚ ይህንን በማረጋገጥ ጣልቃ ያለመግባት መርህ አንድ ሉዓላዊ አገር የውስጥ ጉዳዩን ያለማንም የውጭ ጣልቃ ገብነት መፍታት አንዱና ወሳኙ እንደሆነ ያትታል ያሉ ሲሆን ይህም በአፍሪካ ህብረት የህግ ስርዓት ውስጥ መካተቱንም ገልጸዋል።
በመሆኑም የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ አሳቦት ላሳየው ፍላጎት መንግስት አድናቆት እንዳለው ጠቅሰው አገሪቱ ህግ የማስከበር ዘመቻውን የውስጥ ጉዳይዋ በመሆኑ በራሷ እንደምትፈታውና የሌሎችን ጣልቃ ገብነት የምትሻ ከሆነም መንግስት ጥያቄ ሲያቀርብ ብቻ የሚፈጸም እንደሚሆን አስገንዝበዋል።
በፌደራል መንግስትና በህውሃት ቡድን መካከል የተጀመረው ጦርነት 21ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።[1:06:07 PM]Rekik