EthiopiaNews

የተነሳው ማዕቀብ

በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መነሳቱን የአሜሪካ መከላከያ ንግድ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አስታወቀ።

ዳይሬክቶሬቱ ማዕቀብ መነሳቱን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ወደ ዋሽንግተን አቅንተው ከአሜሪካው አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ተከትሎ ነው።

በቅርቡ በሚወጣ የደንብ ለውጥ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ዝውውር ውስጥ ከሚገኙ አገራት ተርታ ውስጥ እንድትሰረዝ የሚደረግ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ይህ እገዳ በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረው በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ መሆኑንም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews