የንፋስ ኃይል ማመንጫ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን በዛሬው እለት መመረቃቸውን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለዘመኑ የኃይል ዐቅም ተደማሪ የሆነውን ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን መርቀናል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት ይጨምራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይነት ያለው ኃይል ለመገንባት የሚደረገውን ጉዞ ያጠናክራልም ብለዋል።
አክለውም ፕሮጀክቱ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና ያደገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
